- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

ከፖለቲካዊ ነፃነት የሚሻገረው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል

ከፖለቲካዊ ነፃነት የሚሻገረው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል
ሰብስክራይብ

ከፖለቲካዊ ነፃነት የሚሻገረው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል "ሉዓላዊነት ሁለት ዓይነት ነው፤ የውስጥና የውጭ የሚባሉ። የቀድሞ ቅኝ ገዢዎችን መንገድ ብቻ ተከትለን የምንሄድ ከሆነ፣ ለአፍሪካ ሀገራት ችግር ነው የሚሆነው - የፈፀሟቸውም ድርጊቶች ተገቢ አይደሉም በዚህም ታዳጊ ሀገራት ለሉዓላዊነታቸው መታገለል ይኖርባቸዋል።'' ሲሉ በራያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ዶ/ር አሌክሳንደር ሃይማኖት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ሁለት ዐበይት ጉዳዮች በሚዳሰሱበት በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦ በክፍል አንድ፦ “የአፍሪካ ከቀደሙት ቅኝ ገዢዎቿ ሙሉ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገው ትግል አስፈላጊነት” በሚል ርዕስ፣ የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ተፅዕኖዎችን፣ የሳህል ሀገራትን አዲስ ህዝባዊ እንቅስቃሴ እና ዘላቂ የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ነፃነትን የማረጋገጫ መንገዶች ከራያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አሌክሳንደር ሃይማኖት (ዶ/ር) ጋር የተወያየንበት ሲሆን፤

በክፍል ሁለት፦ “የኑክሌር ኤነርጂ ትብብር በብሪክስ ሀገራት መካከል” በሚለው አህጉራዊ አጀንዳ፣ የአፍሪካን የኃይል እጥረት ለመቅረፍ የኒዩክሌር ቴክኖሎጂ ፋይዳ፣ የብሪክስ አባል ሀገራት የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ታዋቂ ተመራማሪ ጌታቸው አዳም ወርቅነህ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንቃኘዋለን።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0