በአዲስ አበባ የሚሸጡ ጥሬ ወተቶች ላይ ካንሰር አምጪና ለተለያዩ በሽታዎች አጋላጭ ንጥረ ነገሮች ተገኙ
16:21 06.10.2026 (የተሻሻለ: 16:24 06.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ የሚሸጡ ጥሬ ወተቶች ላይ ካንሰር አምጪና ለተለያዩ በሽታዎች አጋላጭ ንጥረ ነገሮች ተገኙ
በአዲስ አበባ ከተማ በየመንደሩ ለሽያጭ የሚቀርብ ጥሬ ወተት ላይ የሚጨመሩ ባዕድ ነገሮች መበራከታቸውን የከተማው ግብርና ልማት ኮሚሽን ያካሄደው የዳሰሳ ጥናት ማመልከቱን፤ የሀገር ውስጥ ሚዲያ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኃላፊን ጠቅሶ ዘግቧል።
ኮሚሽኑ ባካሄደው ጥናት በመዲናይቱ 11 ክፍለ ከተሞች ውሀ እንዲሁም ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ መርዛማ ባዕድ ንጥረ ነገሮች ተገኝተዋል ተብሏል።
ኮሚሽኑ ጥናቱን ተከትሎ የቁጥጥር ሥራውን ለማጠናከር የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X