- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

በቀለማት የተጻፈ ማንነት፡- የአፍሪካ ከተሞች እና የግድግዳ ስዕሎች

በቀለማት የተጻፈ ማንነት፡- የአፍሪካ ከተሞች እና የግድግዳ ስዕሎች
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ከተሞች በፍጥነት በማደግ ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት የሕዝብ ጥበብ እና የግድግዳ ስዕሎች የከተሞችን ገጽታ በመቅረጽ፣ የባህርይ መገለጫ በመሆን እና የህብረተሰቡን የጋራ ትዝታ በመጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። በሌላ በኩል፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ ሰፊ የከተማ እድሳት፣ አረንጓዴ ኮሪደሮች እና የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች ልማቶች ከባህላዊ እሴቶችና ከሥነ ጥበብ ስራዎች ጋር ተቀናጅተው የከተማዋን መልክ በማስዋብ ላይ ይገኛሉ።

"...በዚህ ረገድ አርቲስቶች ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላሉ ብዬ አምናለሁ። ከጎዳና ጥበብ እጅግ ማራኪ ከሆኑ ገጽታዎች አንዱ የድንገተኛ መገረም ስሜት መፍጠሩ ነው። ሰዎች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ያልተጠበቀ የግድግዳ ስዕል ሲያጋጥሟቸው፣ ከመደበኛ ኤግዚቢሽኖች ፍጹም በተለየ መንገድ ይማርካቸዋል።" ስትል የቪዥዋል አርቲስቷ ኤፍራታ ብርሃኑ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች ።

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የሕዝብ ጥበብ እና የግድግዳ ስዕሎች በከተሞች መዋቅርና በባህላዊ ማንነት ላይ ያላቸውን አስተዋጽኦ እንዲሁም የኢትዮጵያን አዳዲስ የከተማ ልማት እንቅስቃሴዎች በሁለት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም የእይታ አርቲስት እና የግድግዳ ስዕል ባለሙያ ከሆኑት ከኤፍራታ ብርሃኑ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0