በታንዛንያ የሚካሄደው የኢንተር-ፓርላማ ኅብረት ጉባኤ የሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ገጽታ ያሳድጋል - የሥራ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

በታንዛንያ የሚካሄደው የኢንተር-ፓርላማ ኅብረት ጉባኤ የሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ገጽታ ያሳድጋል - የሥራ ሚኒስትር

የዓለም ፓርላማ መሪዎችን ወደ አሩሻ ማምጣት ታንዛንያንና መስህቦቿን ለማስተዋወቅ "በጣም ትልቅ ዕድል ይፈጥራል" ሲሉ የሥራ ሚኒስትሩ ማሳንጃ ካዶጎሳ ከኢንተር-ፓርላማ ኅብረት (አይፒዮ) ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ጉባኤው የታንዛንያን የበለፀገ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሠረተ ልማት እና ሀገሪቱ ለዓለም ምን ማቅረብ እንደምትችል ለማሳየት ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።

ካዶጎሳ ጉባኤውን ለማስተናገድ ላደረጉት የላቀ ዝግጅት ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰንንም አሞግሠዋል።

 

ታንዛኒያ ከ150 ሀገራት የተወጣጡ 2,000 ልዑካንን አሰባስባ፤ 153ኛውን የኢንተር-ፓርላማ ኅብረት ጉባዔ በአሩሻ እያካሄደች ትገኛለች፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0