- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የሩሲያ-አፍሪካ አዲስ የትብብር ምዕራፍ እና የምግብ ዋስትና በአፍሪካ

የሩሲያ-አፍሪካ አዲስ የትብብር ምዕራፍ እና የምግብ ዋስትና በአፍሪካ
ሰብስክራይብ

“ብዙ ጊዜ የምናየው በሌሎች ነባር ተቋማት ስናይ ከአፍሪካ ጋር ያላቸው ግኑኝነት ለእነሱ ባደላ መልኩ ነው፡፡ ይህንን ማግኘት ከፈለግክ እነኚህን እነኚህን ነገሮች አሳልፈህ ስጥ የሚል እጅ የመጠምዘዝ ነገሮች ናቸው የሚታዩ የነበሩት። የሩሲያን አካሄድ ስንመለከተው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በመነጋገር እና መጨረሻ ላይ በተስማሙባቸው ኤሪያዎች ላይ አብሮ የመስራት እና አብሮ የማደግ ግንኙነቶችን የሚያራምድ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው የያዙት ሩሲያውያን።” ሲሉ ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶስዮሎጂ ት/ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የታሪክ ተመራማሪና ተንታኝ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ሁለት አበይት ጉዳዮች በሚዳሰሱበት በዚህኛው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦ በክፍል አንድ፦ “የፑቲን ንግግር እና የሩሲያ ከአፍሪካ ጋር አብሮ የማደግ ፍላጎት” በሚል ርዕስ፣ የሞስኮ አዲስ የጂኦፖለቲካዊ ትስስር ጥሪ፣ የባለብዙ ዋልታ (Multipolar World) እይታ፣ የታሪክ ወዳጅነት እና ለአህጉሪቱ እድገት የሚያበረክተው አወንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ ከዶ/ር ዘላለም ተፈራ ጋር በሰፊው እንዳስሳለን።

በክፍል ሁለት፦ “የመንግስታት፣ የግል ባለሀብቶች እና የማህበረሰቡ ሚና በምግብ ዋስትና እና ስነ-ምግብ” በሚለው አህጉራዊ አጀንዳ፣ አፍሪካ ሀብቷን ተጥቅማ በምግብ እና በስነ-ምግብ ራስን ለመቻል የሶስቱ አካላት ቅንጅታዊ ሃላፊነት፣ ተጨባጭ የታሪክ ምሳሌዎች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስነ -ምግብ ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር እና ተመራማሪ አዲሱ ፈቃዱ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንቃኘዋለን።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0