ብሪክስ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ቀጣዩን የህዋ ምርምር ምዕራፍ ሊመሩ ይችላሉ - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaብሪክስ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ቀጣዩን የህዋ ምርምር ምዕራፍ ሊመሩ ይችላሉ - ባለሙያ
ብሪክስ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ቀጣዩን የህዋ ምርምር ምዕራፍ ሊመሩ ይችላሉ - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.10.2026
ሰብስክራይብ

ብሪክስ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ቀጣዩን የህዋ ምርምር ምዕራፍ ሊመሩ ይችላሉ - ባለሙያ

ባለፉት 70 ዓመታት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ዕድገቶች ቢመዘገቡም የሰው ልጅ አሁንም በህዋ ምርምር ጅማሮ ላይ በመሆኑ ወደፊት ለመራመድ ጠንካራ ዓለም አቀፋዊ ትብብር ያስፈልገዋል ሲሉ ሩሲያዊው የህዋ ሳይንስ ባለሙያ ማክሲም ሱካኖቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

የሰው ልጅ "ከመነሻው ባሻገር ማየት" ቢያውቅም እስካሁን ግን በሙሉ ልብ ትልቁን እርምጃ መውሰድ አልቻለም ሲሉም አክለዋል። ሳይንቲስቶች እያደገ በመጣው የምርምር ሥራቸው አሁን ባላቸው አቅም ለመረዳት የሚያስቸግሯቸውን ክስተቶች እያገኙ ነው።

"በብሪክስ፣ በሻንጋይ ትብብር ድርጅት እና በሌሎች ወዳጃዊ ተቋማት ማዕቀፍ ሰፋፊ የሳይንሳዊ ህዋ ፕሮግራሞችን ማልማት ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ ትብብር የዓለምን ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እንዲሁም ግዙፍ የአዕምሮ እና የኢንዱስትሪ አቅምን ያቀፈ ነው" ብለዋል።

ባለሙያው ይህንን አስተያየት የሰጡት፤ እ.አ.አ ጥቅምት 4፣ 1957 ሶቪየት ኀብረት በዓለም የመጀመሪውን ሰው ሠራሽ ሳተላይት 'ስፑትኒክ 1' ን በማስወንጨፍ የህዋ ዘመን የተጀመረበትን ቀን በማስመልከት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0