የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለውይይት ዝግጁ ካልሆኑ "ከማዕድ ቤቱ ይውጡ" ሲሉ የአሜሪካን አምባሳደር አስጠነቀቁ

© telegram sputnik_ethiopiaየደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለውይይት ዝግጁ ካልሆኑ "ከማዕድ ቤቱ ይውጡ" ሲሉ የአሜሪካን አምባሳደር አስጠነቀቁ
የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለውይይት ዝግጁ ካልሆኑ ከማዕድ ቤቱ ይውጡ ሲሉ የአሜሪካን አምባሳደር አስጠነቀቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.10.2026
ሰብስክራይብ

የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለውይይት ዝግጁ ካልሆኑ "ከማዕድ ቤቱ ይውጡ" ሲሉ የአሜሪካን አምባሳደር አስጠነቀቁ

​ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ከየካቲት ወር ወዲህ ለአሜሪካ አምባሳደር ሊዮ ብሬንት ቦዜል III "ዲፕሎማሲያዊ ያልሆነ ባህሪ" እና በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን በመጥቀስ ሦስተኛውን ኦፊሴላዊ ዲፕሎማሲያዊ አቤቱታ ማቅረቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሮናልድ ላሞላ ለምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

​"በሁኔታው ተገርሚያለሁ። የንግግር ጊዜ አብቅቷል የሚል ዲፕሎማት ሊኖር አይችልም። መነጋገር የእኛ ሥራ ነው። ስለዚህ እንደ ዲፕሎማት መነጋገር እና ውይይት ማድረግ ካልቻሉ... ከማዕድቤቱቱ ይውጡ" ብለዋል።

​ ግሳጼው የመጣው ቦዜል "የነጮች የዘር ማጥፋት" ጉዳይ ዙሪያ ከሰጡት አስተያየት እና ከአፍሪፎረም ተወካዮች ጋር ካደረጉት ስብሰባ በኋላ፤በፕሪቶሪያ መሠላቸታቸውን ገልጸው፤ አሜሪካ ለደቡብ አፍሪካ ያላት ትዕግስት አልቋል ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0