ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ በድርድር በተመሠረቱ ስምምነቶች የባሕር በር ማግኘት እንድትችል ድጋፍ እንደምታደርግ በድጋሚ አረጋገጠች
19:53 05.10.2026 (የተሻሻለ: 20:04 05.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ በድርድር በተመሠረቱ ስምምነቶች የባሕር በር ማግኘት እንድትችል ድጋፍ እንደምታደርግ በድጋሚ አረጋገጠች
በሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አማካኝነት የወጣው መግለጫ፤ የሶማሊያ ፕሬዛዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ በጋራ ስምምነቶች ለንግድ የባሕር በር ማግኘቷን አትቃወምም ማለታቸውን ተከተሎ የመጣ ነው።
የፕሬዚዳንቱ አስተያየት በሶማሊላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ከሞጋዲሹ ከደረሰበት ጥብቅ ተቃውሞ ጋር የሚቃረን ነው ብሏል።
"የሶማሊላንድ መንግሥት ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሠረተ ትብብር የባሕር በር እንድታገኝ የሚያስችሉ ስምምነቶችን በተከታታይ ሲደግፍ ቆይቷል" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።
ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሉዓላዊነቴን ጥሷል ስትል ሶማሊያ መቃወሟ የሚታወቅ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X