ሁለት አዘጋጆች፣ ሁለት የተለያዩ መስተንግዶዎች፦ የአፍሪካ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በሩሲያ እና በአርጀንቲና ያጋጠማቸውን የተለያየ አቀባበል አጋሩ

ሰብስክራይብ

ሁለት አዘጋጆች፣ ሁለት የተለያዩ መስተንግዶዎች፦ የአፍሪካ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በሩሲያ እና በአርጀንቲና ያጋጠማቸውን የተለያየ አቀባበል አጋሩ

ለቤኒን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ አርጀንቲና ያደረገው ጉዞ ጨርሶ አልጋ በአልጋ አልነበረም።

ብሔራዊ ቡድኑ ከአርጀንቲና ጋር ከሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ አስቀድሞ፤ የ25 ሰዓታት አድካሚ የንግድ በረራ፣ የትጥቅ መጥፋት እና በአንድ ፎቅ የሙቅ ውሃ እጦትን ጨምሮ የሆቴል ችግሮች እንዳጋጠሙት ሜጋ ስፖርት ሚዲያ ዘግቧል።

ጉዞው በልዑኩ ላይ ከፍተኛ ድካም በማስከተሉ፤ አንድ የቪዲዮ ተንታኝ ለአፍታ ራሱን ስቶ የነበረ ሲሆን ቡድኑ ያገኘው የጂም ክፍልም ሁለት ምንጣፎች እና ሁለት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብስክሌቶች ብቻ እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጥ ሳውና የነበረው ነበር።

የሊዮኔል ሜሲ የመሰናበቻ ጨዋታ ነው በተባለው በዚህ ግጥሚያ የሚገኘው ገቢ በሙሉ ወደ አርጀንቲና የእግር ኳስ ማኅበር እንጂ ለቤኒን እንደማይደርስ መታወቁ ደግሞ ነገሩን አክፍቶታል።

ከቡርኪና ፋሶ ጋር መሠል አወዛጋቢ ሁኔታ ተከስቶ ነበር።

በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቆ በሚገኘው ሌላ ስፍራ ግን ናሚቢያ በአዘጋጆቿ በተደረገላት ደማቅ አቀባበል በመልካም ስሜት ተመልሳለች።

መስከረም 23 በየካተሪንበርግ በተደረገው የፊፋ ደረጃ ማሻሻያ ጨዋታ በሩሲያ 6 ለ 0 ቢረቱም፤ የናሚቢያ አሠልጣኝ ኮሊን ቤንጃሚን ስለ ዝግጅቱ እና ስለ አቀባበሉ አድናቆት ብቻ ነው የገለፁት።

"በሩሲያ ያለው የዝግጅት ደረጃ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፤ እንግዶችን የመቀበል ባሕሉም በጣም ከፍተኛ ነው፤ ምንም ዓይነት የማቀርበው ቅሬታ የለኝም" ሲሉም ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopiaሁለት አዘጋጆች፣ ሁለት የተለያዩ መስተንግዶዎች፦ የአፍሪካ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በሩሲያ እና በአርጀንቲና ያጋጠማቸውን የተለያየ አቀባበል አጋሩ
ሁለት አዘጋጆች፣ ሁለት የተለያዩ መስተንግዶዎች፦ የአፍሪካ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በሩሲያ እና በአርጀንቲና ያጋጠማቸውን የተለያየ አቀባበል አጋሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.10.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0