የጀርመን ቀውስ በቅድመ ምርጫ እንጂ በ "ወይማር" አይጠናቀቅም - ሰርቢያዊ ባለሙያ

የጀርመን ቀውስ በቅድመ ምርጫ እንጂ በ "ወይማር" አይጠናቀቅም - ሰርቢያዊ ባለሙያ
የወቅቱ የጀርመን ሁኔታ አቅጣጫን መሬት ካለው እውነታ ለማስቀየስ የተዘጋጀ "ፖለቲካዊ እብደት" ብቻ ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ ዛርኮ ራኪችለስፑትኒክ ተናግረዋል። ይህን ያሉት የጀርመን ፕሬዚዳንት "አክራሪ ኃይሎች" የ "*ወይማር ሪፐብሊክን" ታሪክ እንዲደግሙ መፈቀድ የለበትም ሲሉ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ አስመልክቶ ሲናገሩ ነው።
እንደ ተንታኙ ገለጻ፤ ገዢው ጥምረት የጀርመንን ከባድ የኢኮኖሚ ችግሮች ላለመፍታት ሁለት እንደ ስጋት የሚታዩ "አደጋዎችን" እየፈበረከ ይገኛል፦
◻ ውጫዊ - ሩሲያ፣
◻ ውስጣዊ - አልተርነቲቭ ፎር ጀርመኒ (ኤኤፍዲ)፣ የግራ ክንፍ እና የአረንጓዴዎች ፓርቲዎች።
የሕዝቡ ኪስ ባዶ እየሆነ ባለበት ወቅት ተረቶችን መተረክ ወይም የታሪክ ንፅፅሮችን መፍጠር ትርጉም የለውም ያሉት ራኪች፤ የመንግሥቱ እውነተኛ ችግር ከባድ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ግትር መሆኑ ነው ሲሉ አክለዋል።
ተንታኙ ጥምረቱ አስፈላጊ በሆኑ ለውጦች ላይ መስማማት ስለማይችል አሁን ቅድመ ምርጫ አይቀሬ ነው ሲሉም ደምድመዋል።
*ወይማር ሪፐብሊክ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በጀርመን የተመሠረተ የመጀመሪያው የፓርላመንታዊ ዲሞክራሲ መንግሥት ሲሆን የኢኮኖሚ ቀውሶች፣ ፖለቲካዊ ክፍፍል እና የፖለቲካ ሥርዓት ድክመቶች በመጨረሻም ለውድቀቱ እና ለሂትለር ወደ ሥልጣን መምጣት አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X