ዩክሬን በሩሲያ የሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ ለፈፀመችው ጥቃት ዋጋ ትከፍላለች - ክሬምሊን

ዩክሬን በሩሲያ የሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ ለፈፀመችው ጥቃት ዋጋ ትከፍላለች - ክሬምሊን
የሩሲያ የጦር ኃይሎች የኪየቭ አገዛዝ በሩሲያ የሲቪል ኢኮኖሚ ተቋማት ላይ ላደረሰው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኙ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ፔስኮቭ በመግለጫቸው ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦
ኢስቶንያ በተመለከተ፦ የኢስቶንያ ወታደሮች "ንቁ መከላከል" በሚል ሰበብ ወደ ድንበር መጠጋታቸውን በተመለከተ ከስፑትኒክ ዘጋቢ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ መከላከያ ሚኒስቴር እና ሌሎች የሩሲያ መሥሪያ ቤቶች በሩሲያ ድንበሮች ዙሪያ ያለውን ሁኔታ በትክክል ለመከታተል እና ለመገምገም የሚያስችል አስፈላጊው የመረጃ አቅም አላቸው ብለዋል። “በዚህ አቅም ላይ ምንም አይነት ጥርጣሬ ሊኖር አይገባም” ሲሉም አክለዋል።
🟠 በኪየቭ ስላሉ ዲፕሎማቶች፦ በኪየቭ የሚገኙ ዲፕሎማቶችን ሥራ በተመለከተ ውሳኔ የመስጠት መብቱ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ባላቸው ሀገራት እጅ ነው ሲሉ ፔስኮቭ ተናግረዋል። የሩሲያን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ችላ የሚሉ የአውሮፓ ኅብረት ዲፕሎማቶች ሊከሰቱ ለሚችሉ አደጋዎች ኃላፊነቱን እያወቁ እየወሰዱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
🟠 ስለ ሩሲያ-አሜሪካ የኢነርጂ ትብብር፦ ከአሜሪካውያን አጋሮች ጋር በሚደረጉ ውይይቶች በኢነርጂ ዘርፍ ሊኖር የሚችለው የግንኙነት እና ትብብር ርዕስ በእርግጥም እንደሚነሳ ፔስኮቭ ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X