🪖 ኢስቶንያ "ንቁ መከላከል" በሚል ምክንያት በሩሲያ ድንበር አቅራቢያ የጦር ኃይሏን እያጠናከረች እንደሆነ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia🪖 ኢስቶንያ "ንቁ መከላከል" በሚል ምክንያት በሩሲያ ድንበር አቅራቢያ የጦር ኃይሏን እያጠናከረች እንደሆነ ተዘገበ
🪖 ኢስቶንያ ንቁ መከላከል በሚል ምክንያት በሩሲያ ድንበር አቅራቢያ የጦር ኃይሏን እያጠናከረች እንደሆነ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.10.2026
ሰብስክራይብ

🪖 ኢስቶንያ "ንቁ መከላከል" በሚል ምክንያት በሩሲያ ድንበር አቅራቢያ የጦር ኃይሏን እያጠናከረች እንደሆነ ተዘገበ

የኢስቶንያ ባለሥልጣናት "ንቁ መከላከል" ወደሚል ስትራቴጂ ለመሸጋገር መወሰናቸውን ፋይናንሻል ታይምስ ንግግራቸውን ጠቅሶ ዘግቧል።

በኢስቶንያ አንደኛ ብሪጌድ አዛዥ ኮሎኔል ታርሞ ኩንድላ የሚመራውን ክፍል ከታፓ ከሩሲያ ድንበር 50 ኪሎ ሜትር ብቻ ወደምትርቀዉ ዮህቪ ከተማ ለማዛወር፤ ለወታደሮች አዳዲስ ግዙፍ የመኖሪያ ህንፃዎች እየተገነቡ ይገኛሉ። በተጨማሪም በናርቫ 1,000 ወታደሮችን መያዝ የሚችል የጦር ሠፈር በመገንባት ላይ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ሩሲያ የኔቶ አባል ሀገራትን የማጥቃት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ ቢያስረዱም፤ የምዕራባውያን ፖለቲከኞች ከሀገር ውስጥ ችግሮች የሕዝቦቻቸውን ትኩረት ለማስቀየስ ሲሉ "የሩሲያ ስጋት" እያሉ ሽብር መንዛታቸውን ቀጥለዋል።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ ሩሲያ በምዕራባዊ ድንበሮቿ አቅራቢያ ያልተለመደ የኔቶ እንቅስቃሴ መኖሩን ገልጻለች። ጥምረቱ "የሩሲያን ወረራ መግታት" በሚል እንቅስቃሴዎቹን እያሰፋ ይገኛል። የሩሲያ ባለሥልጣናት በአውሮፓ ውስጥ የሚደረገውን ወታደራዊ ዝግጅት በተመለከተ ስጋታቸውን በተደጋጋሚ ገልፀዋል።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሩሲያ ከኔቶ ጋር በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን፤ ነገር ግን ምዕራባውያን አኀጉሪቱን ወደ ጦረኝነት እየቀየሩ ያሉበትን አካሄድ ማቆም እንዳለባቸው በተደጋጋሚ አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0