የፌደሬሽን ምክር ቤት ሙፈሪሃት ካሚልን አፈ ጉባኤ አድርጎ መረጠ
15:51 05.10.2026 (የተሻሻለ: 15:54 05.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የፌደሬሽን ምክር ቤት ሙፈሪሃት ካሚልን አፈ ጉባኤ አድርጎ መረጠ
በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች ሀገራቸውን ያገለገሉት ወ/ሮ ሙፈሪሃት፤ እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር እንደነበሩ የሚታወቅ ነው።
ከዚህ ቀደም ያገለገሉባቸው የሥልጣን ቦታዎች፦
▪ የቀድሞው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሊቀ መንበር፣
▪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያዋ ሴት አፈ ጉባኤ፣
▪ የሰላም ሚኒስትር።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ፤ የቀድሞውን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ደስታ ሌዳሞን ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X