ኢትዮጵያ የውሃ ልማት ፕሮጀክቶቿ የአባይን ውሃ "የማገድ" ተግባር ናቸው የሚለውን መከራከሪያ ውድቅ አደረገች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የውሃ ልማት ፕሮጀክቶቿ የአባይን ውሃ "የማገድ" ተግባር ናቸው የሚለውን መከራከሪያ ውድቅ አደረገች

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ፤ ኢትዮጵያ ከሉዓላዊ መብቷ፣ ከውሃ ፖሊሲዋ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ሕጎች ጋር በተጣጣመ መልኩ የውሃ ፕሮጀክቶችን ማልማት እንደምትችል ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

የሚኒስትሩ ቁልፍ ንግግሮች፦

የግብፅ ፖሊሲ አውጪዎች የአስዋንን ከፍተኛ ግድብ ታሪክ መለስ ብለው በመመልከት፤ "ከግንባታው በፊት ኢትዮጵያ ተማክራ እንደነበር ማጤን" አለባቸው።

ሚኒስትሩ አባይ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የብቻ ይዞታ ተደርጎ ሊወሰድ እንደማይችል የገለጹ ሲሆን ኢትዮጵያ በላይኛው ተፋሰስ የምትገኝ ሀገር እንደመሆኗ መጠን የውሃ ሀብቷን የማልማት መብት እንዳላት አስምረውበታል።

ግብፅ "ቅድመ-ፈቃድ" በሚለው አቋሟ ላይ ሙጥኝ ማለቷ አሁንም ጊዜ ባለፈበት የአባይ አስተዳደር እና በቅኝ ግዛት ዘመን የተደረጉ ስምምነቶች ላይ ጥገኛ ሆና መቅረቷን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ገልጸዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0