ምዕራባውያን ልዩነቶችን በመጠቀም የበላይነታቸውን ለማስቀጠል እየሞከሩ ነው - አልጄሪያዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaምዕራባውያን ልዩነቶችን በመጠቀም የበላይነታቸውን ለማስቀጠል እየሞከሩ ነው - አልጄሪያዊ ባለሙያ
ምዕራባውያን ልዩነቶችን በመጠቀም የበላይነታቸውን ለማስቀጠል እየሞከሩ ነው - አልጄሪያዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.10.2026
ሰብስክራይብ

ምዕራባውያን ልዩነቶችን በመጠቀም የበላይነታቸውን ለማስቀጠል እየሞከሩ ነው - አልጄሪያዊ ባለሙያ

​የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት መድረክ ያደረጉትን ንግግር አስመልክተው አልጄሪያዊው የፖለቲካ ሳይንቲስት ኢዜዲን ኑሜሪ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ ብሪክስ፣ የሻንጋይ የትብብር ድርጅት እና ሌሎች ምዕራባዊ ያልሆኑ ተቋማት እየጠናከሩ በመምጣታቸው የምዕራባውያን ተፅዕኖ እየቀነሰ ይገኛል።

​ኑሜሪ፣ ምዕራባውያን ሀገራት የፖለቲካ ተፅዕኖአቸውን ለማስቀጠል ሲሉ በተለይም በአረብ ሀገራት ውስጥ ልዩነቶችን በማስፋት፣ ቀውሶችን በመቀስቀስ እና አለመረጋጋትን በማፋፋም ምላሽ እየሰጡ መሆናቸውን አንስተዋል።

​እነዚህ ጣልቃ ገብነቶች የተመረጡ የፖለቲካ አካላትን መደገፍን እና የጦር መሣሪያ ማቅረብን ሊጨምሩ እንደሚችሉና በግልጽ የሚደረጉ የመቻቻል ጥሪዎች ግን ሰፊ የጂኦፖለቲካ ፍላጎቶችን ለመሸፈን የሚያገለግሉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

​ ባለሙያው አክለውም፣ "ለብሪክስ እና ለሻንጋይ የትብብር ድርጅት በሂደት ላስመዘገቡት እድገት ምስጋና ይግባና፣ ፖሊሲዎችን የሚያወጡትና መፍትሄዎችን የሚያመነጩት ምዕራባውያን ሀገራት ብቻ ያልሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሯል" ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0