- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና እና የፖሊሲ ማዕቀፎች ውህደት

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና እና የፖሊሲ ማዕቀፎች ውህደት
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ለአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ከመሆኑ ባለፈ፣ የንግድ ኮሪደሮችን እና የገበያ ትስስርን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ አለው። በሌላ በኩል፣ ሀገራት የሚከተሏቸው የፖሊሲ ማዕቀፎች እና ደንቦች አለመጣጣም ለቀጣናው የንግድ ውህደት ትልቁ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል።

ትልቁ የአፍሪካ ኮንቲኔንታል ፍሪ ትሬድ ኤሪያ ኢምፕሊመንት እንዲያደርግ... አንደኛ ሀገራት የሚከተሏቸው ማዕቀፎች፣ ፖሊሲ የምንለው ደንቦች፣ እሱን ማጣጣም ያስፈልጋል። ያን ለማድረግ አሁን አንድ ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፤ በርግጥ ሙከራዎችም አሉ። ግን እስቲል ትልቁ ማነቆ እሱ ነው።"

— ተስፋዬ ቦይሳ፣ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የባለብዙ ወገን ተቋማት ተመራማሪ

በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን የእርስ በርስ ንግድ፣ የንግድ ኮሪደሮች እና የAfCFTA ትግበራ ውስብስብነት እንዲሁም የፖሊሲ ማዕቀፎችን ማጣጣም የሚጠይቁ ጉዳዮችን በሁለት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የባለብዙ ወገን ተቋማት ተመራማሪ የሆኑት ከተስፋዬ ቦይሳ ጋር ቆይታ አድርገናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0