ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የነፋስ ደህንነት መስፈርቶችን የሚያስገድዱ የሕንፃ ደንቦችን አሻሻለች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የነፋስ ደህንነት መስፈርቶችን የሚያስገድዱ የሕንፃ ደንቦችን አሻሻለች

 

ማሻሻያው፣ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን፣ በኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመሪነት ሚና የተከናወነ መሆኑን የሀገር ውስጥ የግል ሚዲያ ዘግቧል።

 

ስለደንቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

 

🟠 ሕንፃዎች የመሬት እንቅስቃሴዎችን የመቋቋም አቅማቸው እንዲረጋገጥ ጥብቅ መመዘኛዎች ተቀምጠዋል።

 

🟠 የክልሎችን የንፋስ ስርጭት የሚያሳዩ ካርታዎችን መሠረት ያደረገ ትክክለኛ መረጃ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጓል።

 

🟠 እንደ “ካርበን-ፋይበር” እና “ብረት-ፋይበር” ያሉ መገንቢያ ቁሳቁሶች አጠቃቀምን የሚቆጣጠሩ መመሪያዎች አሉት።

 

🟠 በ1975፣ በ1987 እና በ2007 ዓ.ም ከተደረጉ ማሻሻያዎች በመቀጠል አራተኛው የሕንፃ ሕግ ማሻሻያ ነው።

 

ሀገሪቱ በ5 ዓመታት ውስጥ ለመገንባት ላቀደችው 1.5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ጥብቅ የጥራት ቁጥጥር እና የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊ መሆኑ ተጠቅሷል።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0