ኢትዮ-አሜሪካዊቷ ደራሲ ማዓዛ መንግሥቴ የ2026 የማክአርተር ፈሎውሺፕ አሸናፊ ሆነች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮ-አሜሪካዊቷ ደራሲ ማዓዛ መንግሥቴ የ2026 የማክአርተር ፈሎውሺፕ አሸናፊ ሆነች
ኢትዮ-አሜሪካዊቷ ደራሲ ማዓዛ መንግሥቴ የ2026 የማክአርተር ፈሎውሺፕ አሸናፊ ሆነች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.10.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮ-አሜሪካዊቷ ደራሲ ማዓዛ መንግሥቴ የ2026 የማክአርተር ፈሎውሺፕ አሸናፊ ሆነች

 

ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ 800 ሺህ ዶላር የሚያስገኘውን የ2026 የማክአርተር ፈሎውሺፕ ካሸነፉ 20 አርቲስቶች፣ ደራሲያን፣ ምሁራን እና ሳይንቲስቶች መካከል አንዷ ሆና ተመርጣለች።

 

ደራሲዋ የምትታወቅባቸው ሥራዎች፡-

 

▪ የመጀመሪያ ልቦለዷ፦ "ቤኒዝ ዘ ላየንስ ጌዝ” (Beneath the Lion’s Gaze) የተሰኘው የመጀመሪያው የልቦለድ መጽሐፏ እ.ኤ.አ. በ2010 የታተመ ነው።

 

▪ ታዋቂው ሥራዋ፦ “ዘ ሻዶው ኪንግ” (The Shadow King) እ.ኤ.አ. በ2019 የታተመው ሲሆን በጣሊያን የኢትዮጵያ ወረራ ወቅት የነበረውን የሴት አርበኞችን ሚና እና ታሪክ ወደ ሕይወት አምጥቷል።

 

▪ ዝግጅት፦ "አዲስ አበባ ኑዋር” (Addis Ababa Noir) የተሰኘ የብዙ ደራሲያን አጫጭር ታሪኮች ስብስብ መጽሐፍ በአርትኢነት አሳትማለች።

 

▪ ሌሎች፦ ከመጻሕፍት ባሻገርም የተለያዩ አጫጭር ታሪኮችን፣ ድርሰቶችን እና መጣጥፎችን በማስነበብ ትታወቃለች፡፡

 

▪ የጽሑፎቿ ጭብጥ፦ ታሪክን፣ ትዝታን እና የፈጠራ አስተሳሰብን በማጣመር የፖለቲካ ግጭቶች እና ብጥብጦች የሚያስከትሉትን ሞራላዊ እና ሰብዓዊ ጉዳቶች በጽሑፎቿ ታሳያለች።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0