'ዓለም አቀፉ ስርዓት የአፍሪካን እያደገ የመጣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተፅዕኖ ማወቅ አለበት' - ናይጄሪያዊ ተነታኝ
15:25 04.10.2026 (የተሻሻለ: 15:34 04.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
'ዓለም አቀፉ ስርዓት የአፍሪካን እያደገ የመጣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተፅዕኖ ማወቅ አለበት' - ናይጄሪያዊ ተነታኝ
"ባለ ብዙ-ዋልታ የዓለም ስርዓት ለአፍሪካ ሀገራት በርካታ የአጋርነት፣ የኢንቨስትመንት፣ የገበያ አማራጮችን እና የላቀ የመደራደር አቅምን ሊሰጣቸው ይገባል" ሲሉ የዓለም አቀፍ ደህንነት ተንታኝ ዲክሰን ኦሳጂ፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ስለ አዲሱ የዓለም አቀፍ ስርዓት በቫልዳይ የውይይት መድረክ ላይ ያደረጉትን ንግግር በማስመልከት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ውክልና
አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር ይገባታል ያሉት ባለሙያው፣ ናይጄሪያ በሊበሪያ እና በኮንጎ በነበራት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሚና ምክንያት ጠንካራ የመጠየቅ መብት አላት ብለዋል።
የፍላጎቶች ሚዛን
ለአፍሪካ ዋነኛው አደጋ "በታላላቅ ልዕለ ኃያልን ሀገራት መካከል ለሚደረገው ጂኦፖለቲካዊ ውድድር የመጫወቻ ሜዳ" መሆን ነው ያሉት ኦሳጂ፤ ሌሎች ስጋቶች ደግሞ የዕዳ ጫና፣ የጥሬ ዕቃዎች ላይ ጥገኝነት፣ ደካማ ተቋማት እና የቴክኖሎጂ ጥገኝነት እንደሆኑ አስምረውበታል።
የሩሲያ-አፍሪካ ትብብር
ተንታኙ በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያለውን ትብብር በማጉላት "አፍሪካ የራሷን የቴክኒክ ክህሎት ማሳደግ አለባት" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች፡-
🟠 የቴክኖሎጂ ሽግግር፣
🟠 የሀገር ውስጥ ምርታማነት፣
🟠 የግብርና እና የኢነርጂ መሠረተ ልማት፣
🟠 የመከላከያ ሥልጠና፣
🟠 ትምህርት እና
🟠 ጤና ጥበቃ።
"ዋናው ፕሮጀክት ለአፍሪካውያን የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የሀገር ውስጥ ክህሎትን መገንባት እና በውጭ አጋሮች ላይ ያለውን የረጅም ጊዜ ጥገኝነት መቀነስ ነው" ያሉት ተነታኙ፤ የፑቲን ንግግርም ከዚህ አጀንዳ ጋር "የሚጣጣም" መሆኑን ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X