የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም ከ69% በላይ አድጓል – የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም ከ69% በላይ አድጓል – የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

የ"ኢትዮጵያ ታመርት" ንቅናቄ እና "የብሔራዊ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ምክር ቤት" በዘርፉ ያሉ እንቅፋቶችን በማስወገድ የመሠረተ ልማትና የግብዓት ችግሮችን እየፈቱ በመሆናቸው ይህ ዕድገት መምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባልሥልጣን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል።

በመንግሥት የተወሰዱ ዋና ዋና እርምጃዎች እና ውጤታቸው፦

 

🟠 የኤሌክትሪክ፣ የውሃ፣ የካፒታል እና የግብዓት ችግሮች በመፈታታቸው ተዘግተው የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ ተመልሰዋል።

 

🟠 የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቅረፍ የመለዋወጫ ዕቃዎችን፣ ማሽኖችንና ቴክኖሎጂዎችን ለማስገባት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

 

🟠 በጨርቃ ጨርቅ፣ በምግብና መጠጥ፣ በብረታ ብረት እና በቆዳ ዘርፎች የተኪ ምርት ምርቶች ተስፋፍተዋል።

 

🟠 ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 5.9 ቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል።

 

በ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ የኢንዱስትሪ የውጭ ንግድ ገቢን ወደ 9 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ፣ 5 ሚሊዮን የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እና የማኑፋክቸሪንግን የጂዲፒ ድርሻ ወደ 17.2 በመቶ ለማሳደግ ታቅዷል።

 

  ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0