ትምህርት ሚኒስቴር በ1.4 ቢሊዮን ብር በባሕር ዳር የሚያስገነባው ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመረ
13:05 04.10.2026 (የተሻሻለ: 13:14 04.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ትምህርት ሚኒስቴር በ1.4 ቢሊዮን ብር በባሕር ዳር የሚያስገነባው ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመረ
ብቁና ተወዳዳሪ ትውልድ የሚያፈሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እየተገነቡ እንደሚገኙ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በማሥጀመሪያ ሥነ–ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።
የሚኒስትሩ ንግግር ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 በ1.4 ቢሊዮን ብር የሚገነባው አዳሪ ትምህርት ቤቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡
🟠ከ2020 ዓ.ም. ጀምሮ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል፡፡
🟠 በክልሉ፣ በሰሜኑ ግጭት ወቅት የወደሙ 45 1ኛ ደረጃ እና 7 የ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መልሰው ተገንብተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X