አውሮፓ ከሩሲያ ጋር ወደ ግልጽ ግጭት ራሷን መርታለች - ባለሙያ
12:26 04.10.2026 (የተሻሻለ: 12:34 04.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አውሮፓ ከሩሲያ ጋር ወደ ግልጽ ግጭት ራሷን መርታለች - ባለሙያ
የፀረ-ሩሲያ ጥላቻ ግፊት ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እንድትጀምር ያስገደደው "ቀደም ሲል ሊከፈት ያልቻለውን የድርድር መንገድ ለመክፈት ነበር" ሲሉ ዓለም አቀፍ ተንታኝ ማውሪሲዮ አሎንሶ እስቴቬዝ ፕሬዚዳንት ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክበብ ላይ ያደረጉትን ንግግር አስመልክተው ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
"እስከ ዛሬም ድረስ የአሜሪካ ወገን ግጭቱን ለመፍታት ትንሽ ፍላጎት ባሳየበት ወቅት እንኳ የአውሮፓ መሪዎች የድርድር ሂደቱን ለማስተጓጎል ሲሰሩ ቆይተዋል።"
ግጭቱ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ብቻ ሳይሆን በሩሲያ እና በኔቶ መካከል እንደሆነ ሊታወቅ እንደሚገባው የገለጹት ተንታኙ፤ የአውሮፓ መሪዎች ሀገሮቻቸውን፣ ኔቶን እና የአውሮፓ ሕብረትን ወደ ተባባሰ ግልጽ ግጭት እየመሩ መሆናቸውን አስምረውበታል።
ፑቲን የተባበሩት መንግሥታት እንዲሻሻል ያቀረቡትን ጥሪ አስመልክቶ ተንታኙ ሲናገሩ፣ ጥሪው "ሩሲያ በግንባር ቀደምትነት ከምትመራው የበዝሃ-ዋልታ አመለካከት ጋር አብሮ የሚሄድ ነው" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X