የአፍሪካ ታላላቅ እቅዶች ወደ ተግባር መተርጎም አለባቸው – የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ታላላቅ እቅዶች ወደ ተግባር መተርጎም አለባቸው – የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር

 

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማሐሙድ አሊ ዩሱፍ በግብፅ በተካሄደው የ”አላሜይን አፍሪካ ፎረም” ላይ ባደረጉት ንግግር፣ አኅጉሪቱ የታቀዱ ታላላቅ ራዕዮችን ወደ ተግባር መለወጥ እንዳለባት አሳስበዋል።

 

 “አፍሪካ የራዕይ አልያም የዓላማ እጥረት የለባትም። ዋናው አስፈላጊው ነገር የተወጠኑ ግዙፍ እቅዶችን ወደተዘጋጁ፣ ፋይናንስ ወደተደረገላቸው፣ ወደተተገበሩ እና ወደተሳኩ ፕሮጀክቶች በወጉ የመቀየር አቅም ነው።”

አፍሪካ እሴት ለመፍጠር፣ ኢንዱስትሪዎችን ለመገንባት፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠርና የኢኮኖሚ ጥንካሬዋን ለማጠናከር ሀብቷን መጠቀም እንዳለባት ነው ማሐሙድ አሊ ዩሱፍ ያስገነዘቡት።

“አፍሪካ ማምረት የምትችለውን ምግብ፣ ማምረት የምትችለውን መድኃኒት እና ከራሷ ጥሬ ዕቃ ሊሠሩ የሚችሉ ምርቶችን አሁንም ከውጭ ማስመጣቷ አልቀረም።”

“አላሜይን አፍሪካ ፎረም” በግብፅ መንግሥት፣ በአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ እና በአፍሪካ ሕብረት የልማት ኤጀንሲ ጥረት በ2026 የተመሠረተ ቋሚ አኅጉራዊ የንግድ መድረክ ነው። በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተገናኝተው የአኅጉሪቱን የኢኮኖሚ፣ የንግድ፣ የዲጂታልና የኢንዱስትሪ እድገት የሚያፋጥኑ ውሳኔዎች ላይ ይመክራሉ። ፎረሙ ከመስከረም 22 እስከ 24 በኒው አላሜይን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0