የፑቲን የቫልዳይ ንግግር ሩሲያ ለአፍሪካ ልማት ቅድሚያ እንደምትሰጥ ያመላክታል - ደቡብ አፍሪካዊ ተመራማሪ
የፑቲን የቫልዳይ ንግግር ሩሲያ ለአፍሪካ ልማት ቅድሚያ እንደምትሰጥ ያመላክታል - ደቡብ አፍሪካዊ ተመራማሪ
ከተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ባሻገር፣ የአፍሪካ ተፅዕኖ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ፣ የንግድ፣ የቴክኖሎጂ እና የሕግ ሥርዓቶች ውስጥ ጠንካራ የጋራ ወክልና ሊኖረው ይገባል ሲሉ የብሪክስ የምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ዲላን ማንጌና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ብሪክስ እና መሰል የደቡባዊ ዓለም ተቋማት የአፍሪካ ሀገራት የልማት ቅደም ተከተሎቻቸውን የሚያሰፉበት እና የሚያሳውቁበት ተጨማሪ መድረክ ይሆናሉ።"
በሀገር ውስጥ ምርት፣ በመሠረተ ልማት፣ በቴክኒክ ትምህርት፣ በምርምር ተቋማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ያካተተው የሩሲያ እና አፍሪካ የልማት አጋርነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ማንግና ጠቁመዋል።
አፍሪካውያን ኩባንያዎች የኮንትራት ተቀባይ ወይም የጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች ብቻ ሆነው ከመቅረት ይልቅ አቅማቸውን የሚያሳድጉበት የጋራ ኢንተርፕራይዞች ሊፈጠሩ ይገባል ያሉት ተመራማሪው፤ የአፍሪካውያን ባለቤትነት፣ የአቅም ግንባታ እና የሚለካ እሴት ሀገር ውስጥ ማስቀረት የሂደቱ ዋና መመሪያዎች ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከሩሲያ እና ከደቡባዊ ዓለም አካላት ጋር የሚደረጉ አጋርነቶች ለሥልጠና፣ ለመሠረተ ልማት፣ ለሳይበር ደህንነት እና ለቴክኖሎጂ ትልቅ ቦታ አላቸው፤ ስምምነቶች የእውቀት ሽግግርን እና የሀገር ውስጥ አቅም ግንባታን የሚያካትቱ ከሆነ ሲሉ አክለዋል።
አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ነፃነቷን ጠብቃ የተኩስ አቁም ዲፕሎማሲን፣ ቅድመ-መከላከል እንቅስቃሴዎችን፣ የሰብአዊ እርዳታ ተዳራሽነትን እና በድርድር የሚደረጉ ስምምነቶችን ማፋጠን ትችላለች ሲሉ ማንግና ገልጸዋል።
"ዋናው ዓላማ የአፍሪካ ሀገራት ሕግ ተቀባይ ብቻ ከመሆን አልፈው ሕግ አውጪ እና አጀንዳ ቀራጭ የሚሆኑበትን ዓለም አቀፍ ሥርዓት መፍጠር መሆን አለበት።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X