ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት በኢትዮጵያ አዲስ የንግድ ሥራ ዕቅድ ውድድር ይፋ አደረገ
16:25 03.10.2026 (የተሻሻለ: 16:34 03.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት በኢትዮጵያ አዲስ የንግድ ሥራ ዕቅድ ውድድር ይፋ አደረገ
ድርጅትቱ (አይኤልኦ) በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞችና አስተናጋጅ ማኅበረሰቦች የሚሆን አዲስ የንግድ ሥራ ዕቅድ ውድድር ምዕራፍ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።
የፕሮግራሙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
3,000 ለሚሆኑ አዳዲስ እና ነባር የንግድ ሥራ ፈጣሪዎች እድሉ ይመቻቻል።
በሱማሌ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በአማራ ክልሎች ይተገበራል፡፡
ጅጅጋ፣ ከብሪበያህ፣ አሶሳ እና ዳባት የስደተኞች ካምፕ እና አካባቢዎችን ያካትታል።
ለተሳታፊዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች፦
🟠 የሥራ ፈጠራ እና የፋይናንስ ትምህርት ሥልጠና፣
🟠 የንግድ ሥራ ዕቅድ ዝግጅት ድጋፍ፣
🟠 የአሠልጣኝነት እና የምክር አገልግሎት፣
🟠 የፋይናንስ አቅርቦት ድጋፍ፣
🟠 ንግድን ሕጋዊ የማድረግ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣት እና የክህሎት ማሣደጊያ ድጋፎች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X