አፍሪካ "ራሷን ሙሉ በሙሉ መወከል ካልቻለች ራሷን መመገብ አትችልም፡ የማላዊ ባለሙያ
አፍሪካ "ራሷን ሙሉ በሙሉ መወከል ካልቻለች ራሷን መመገብ አትችልም፡ የማላዊ ባለሙያ
አፍሪካ የማዳበሪያ እና የዘር፣ እንዲሁም የመሠረታዊ ምግብ እና የነዳጅ አቅርቦቶችን ጨምሮ ሀገራት "የእሴት ሰንሰለቶችን ሲረከቡ"፣ የእርዳታና የወጪ ገቢ ሂሳቦችን ሲቀንሱ እና በአንድ አህጉር ደረጃ ለመደራደር "እርስ በርስ ሲደጋገፉ" የራሷን ጥንካሬዎች "ማወቅና መንቃት አለባት" ሲሉ በሁለገብ የአፍሪካ ግብርና ልማት ፕሮግራም መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ቡድን ሰብሳቢ ቺኮንዲ ቻብቩታ-ምካዋ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
"በዚያ ጊዜ ስለ ሉዓላዊነት በቀላሉ ከመናገር ባሻገር በተግባር የሚኖር እውነታ ለማድረግ እድሉ ይኖረናል" ብለዋል።
ኤል ኒኞ
በደቡባዊ አፍሪካ ድርቅን እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ጎርፍን የሚያመጣው ከፍተኛ የኤል ኒኞ ክስተት እየቀረበ ሲመጣ፣ ስኬቱ የሚሆነው የመንግሥታት ቃልኪዳኖች "በብሔራዊም ሆነ በቀጣና (ወረዳ) ወይም በሌሎች ዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች" በገንዘብ ተደግፈው ቅድሚያ መሰጠታቸው ላይ ነው ሲሉ ቻብቩታ-ምካዋ አብራርተዋል።
የአየር ንብረት ቀውስ
አፍሪካ ለአየር ንብረት ቀውሱ መከሰት ምንም አይነት አስተዋጽኦ ባታደርግም፣ "አርሶ አደሮቿ ግን የመጀመሪያውን ዋጋ ይከፍላሉ" ያሉት ባለሙያዋ፣ የመቋቋም አቅም መሠረት መሆን እንዳለበት እና መንግሥታት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት እና ድርጅቶች ለማላመድ የሚሆን ፋይናንስ ለማግኘት በጋራ መግፋትና መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
"በተናጠል መሥራት የትም አላደረሰንም። ስለዚህ አብሮ የመሥራትን አማራጭ እንሞክረው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X