- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ስለአዲሱ የዓለም ሥርዓት ከቫልዳይ የተሰማው መልዕክት

ስለአዲሱ የዓለም ሥርዓት ከቫልዳይ የተሰማው መልዕክት
ሰብስክራይብ
ፕሬዚዳንት ፑቲን ዓለም ወሳኝ የእጥፋት ነጥብ ላይ መድረሷን ገልጸው፤ ዓለማችን ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ደህንነትንና የዓለም አቀፍ ኃይልን ሊቀርጽ የሚችልበት አዲስ የቴክኖሎጂ ዘመን ላይ መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል።

ምዕራባውያን ሌላ ጠንካራ አገር እንዲፈጠር አይፈልጉም፤ ቢፈጠርም በተለያየ መልኩ ያዳክሙታል። ሩሲያ ከናቶ እና ከምዕራቡ ዓለም ጋር በዩክሬን የገጠማት ጦርነት አንዱ ማሳያ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ አፍሪካም በኢኮኖሚና በሌሎች ዘርፎች ራሴን ልቻል የሚለ ሀገር ብቅ ቢል በተለያዩ መንገዶች ለማዳከም የሞክራሉ” ሲሉ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

🎙የዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክለብ 2026 የመዝጊያ ስነ-ሰርዓት ላይ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር፣ ከባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት እና ለአፍሪካ ከሚኖረው ፋይዳ አንፃር የምንቃኝበት ነው። ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ጋር አውርተናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0