የሴንተር-2026 ወታደራዊ ልምምድ ትኩረት ከውጭ የሚሰነዘር ጥቃት በመመከት ላይ ነው - ፑቲን
20:25 02.10.2026 (የተሻሻለ: 20:34 02.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሴንተር-2026 ወታደራዊ ልምምድ ትኩረት ከውጭ የሚሰነዘር ጥቃት በመመከት ላይ ነው - ፑቲን
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንደገለጹት የ"ሴንተር-2026" እና የጋራ ደህንነት ስምምነት ድርጅት ኢንተራክሽን-2026 ወታደራዊ ልምምዶች ዋና ዓላማ ከውጭ የሚሰነዘሩ ወታደራዊ ስጋቶችን መመከት የሚያስችል የወታደራዊ ዕዝ እና የሠራዊት ዝግጅትን ማጠናከር ነው።
"ሁሉም ተግባራት እየተከናወኑ ያሉት ከልዩ ወታደራዊ ዘመቻው የተገኙ ተሞክሮዎችን እና ልምዶችን መሠረት በማድረግ ነው" ሲሉ ፑቲን በቼባርኩል ማሠልጠኛ ስፍራ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በ11 ማሠልጠኛ ስፍራዎች እና በካስፒያን ባህር በሚካሄደው በዚህ ልምምድ ላይ ከ47,000 በላይ ወታደሮች የተሳተፉ ሲሆን አዳዲስ የጦር መሣሪያዎች እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችም በተግባር እየተሞከሩ ይገኛሉ።
በተጨማሪም ፑቲን የውጭ ሀገራትን ሰፊ ተሳትፎ አጉልተው የገለጹ ሲሆን የ55 ሀገራት ልዑካን ቡድኖች በልምምዱ ላይ ለመገኘት ወደ ሩሲያ መምጣታቸውን አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X