የሩሲያ-አፍሪካ አብሮ የመበልጸግ የፑቲን ሐሳብ በጣም ጥሩ እይታ ነው – ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ-አፍሪካ አብሮ የመበልጸግ የፑቲን ሐሳብ በጣም ጥሩ እይታ ነው – ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክለብ “ከአፍሪካ ጋር አብረን ለመበልጸግ በጋራ እንሠራለን” ሲሉ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የታሪክ ተመራማሪ ዶ/ር ዘላለም ተፈራ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን አጋርተዋል፡፡

ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በመደጋገፍ፣ በአብሮነት እንዲሁም የህዝቦችን የኑሮ ደረጃ በሚያሻሽሉ ጉዳዮች ላይ በመመካከር ላይ የተመሠረተ መሆኑን በማስታወስ የፑቲን አብሮ የመበልጸግ ሐሳብ ጥሩ እይታ መሆኑን ገልጸዋል።

“የሁለቱ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ጠበብቶች በአንድ መድረክ ላይ ቁጭ ብለው ተወያይተው የሚወስኑት እንጂ ከአንድ ማዕከል ብቻ ይህንን ተቀበል ብሎ የሚላክ አይደለም” ሲሉ የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት አዛዥና ታዛዥ እንደሌለበት አስረድተዋል።

በሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነት ውስጥ እንደ ሌሎች ወገኖች እጅ የመጠምዘዝ አካሄዶች እንደማይታ ዶ/ር ዘላለም አብራርተዋል፡፡

“የሩሲያ ግንኙነት ይህንን አያበረታታም። በመነጋገር እና መጨረሻም በተስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ አብሮ የመሥራትና የማደግ ግንኙነቶችን አሸናፊ የሚያደርግ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው። ስለዚህም ፕሬዝዳንት ፑቲን ያንን ነው ያስተጋቡት” ብለዋል።

የሞስኮ የፖሊሲ አቅጣጫ የአፍሪካ እና ሩሲያን ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያጠናክረውና የዲፕሎማሲ ግንኙነቱንም እንደሚያጠብቀው እምነታቸውን ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0