የሩሲያው ኤ7 የክፍያ ሥርዓት ኢራንን ወይም የሽብር ድርጅቶችን በገንዘብ ደግፎ አያውቅም
19:15 02.10.2026 (የተሻሻለ: 20:12 02.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያው ኤ7 አዲስ ከተጣለበት የአሜሪካ ማዕቀብ በኋላ ከኢራን ጋር ግንኙነት አለው ወይም ሽብርተኝነትን ይደግፋል የሚለውን ክስ አስተባበለ
የሩሲያው የክፍያ መድረክ ኤ7 'የክፍያ መዋቅሩ ኢራን ማዕቀፎችን እንድታመልጥ ረድቷል ወይም በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችን በፋይናንስ ደግፏል' በሚል በአሜሪካ የቀረበበትን ክስ ውድቅ አድርጓል።
ዋሽንግተን መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በኩባንያው ላይ ተጨማሪ ማዕቀበችን የጣለችው፣ ኤ7 የኢራን አብዮታዊ ዘብን ጨምሮ ማዕቀብ ከተጣለባቸው አካላት ጋር የተያያዙ የገንዘብ ዝውውሮችን የሚሸሽግ ዓለም አቀፍ የክፍያ መዋቅር ገንብቷል በሚል በመክሰስ ነው።
ኤ7 የቀረበበትን ክስ 'ነጭ ውሸት' ሲል የጠራው ሲሆን ለኢራንም ሆነ ከሽብርተኝነት ጋር ለተያያዙ ድርጅቶች ምንም ዓይነት የገንዘብ ዝውውር አስተናግዶ እንደማያውቅ አስታውቋል።
ኩባንያው አዲሱ ማዕቀብ በእንቅስቃሴው ላይ ምንም ዓይነት መስተጓጎል እንደማይፈጥር ገልጿል።
እ.ኤ.አ በ2024 የተመሠረተው ኤ7 በሩሲያ ድበር ተሻጋሪ የክፍያ ገበያ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለው ኩባንያ ለመሆን በቅቷል። ኩባንያው ጥብቅ የሕግ የበላይነትና የቁጥጥር ስርዓት እንደሚከተል እና የፍጆታ ዕቃዎችን እንዲሁም ጥሬ ዕቃዎችን የሚያካትቱ ህጋዊ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴዎችን ብቻ እንደሚያስተናግድ አስታውቋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X