የሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነት ከቅኝ ግዛት ነፃነት በፊት የጀመረና ታሪካዊ መሠረት ያለው ነው – ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ
17:37 02.10.2026 (የተሻሻለ: 17:44 02.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነት ከቅኝ ግዛት ነፃነት በፊት የጀመረና ታሪካዊ መሠረት ያለው ነው – ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ
የአፍሪካ ሀገራት በቀኝ ግዛት ሥር በነበሩበት ወቅት ሩሲያ ለአፍሪካ የነፃነት ታጋዮች ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን ታደግ እንደነበር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የታሪክ ተመራማሪ ዶ/ር ዘላለም ተፈራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
“የሥልጠና ድጋፍ፣ የመሣሪያ ድጋፍ እና በአጠቃላይ የነጻነት እሳቤ (የጽንሰ-ሐሳብ) ድጋፍ ታደርግ ነበር። እና በዚያ ጊዜ የተደረገው ድጋፍ በጣም ከፍተኛ ነው” ብለዋል።
ዶ/ር ዘላለም፣ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክለብ በነበራቸው ቆይታ፤ ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር የሚኖራት ግንኙነት ቅኝ ገዥዎች እንዳደረጉት "የማትረፍ ወይም የመዝረፍ" እንደማይሆን አጽንኦት የሰጡበትን ንግግር ታሪካዊ ሀቅን በመምዘዝ አስረግጠዋል፡፡
“ከትግል በኋላ ብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ገና አስተዳደራቸው በደንብ ያልቆመ፣ ያልተረጋጋ ነበረ። በትምህርት ወደፊት አልገፉም፤ በኢኮኖሚ ራሳቸውን አልቻሉም፤ በብዙ ነገር ውጥረት ላይ በነበሩበት ወቅት ላይ የሶቪዬት ሕብረት እርዳታ በጣም ከፍተኛ ነበር” ብለዋል።
የታሪክ ተመራማሪው፣ ሩሲያ በዓለም አቀፍ መድረክ ድምፅ ከመሆን ባለፈ ከአፍሪካ ጋር ምንም ዓይነት የቀኝ ግዛት ታሪክ እንዳልነበራት በመጠቆም ሩሲያ እና አፍሪካ ወደፊት አብሮ የሚያሠራቸው ታሪካዊ መሠረት እንዳላቸው አስረድተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X