ከባዶ የሰላም ወሬ ይልቅ ወደ ተጨባጭ እርምጃ መሸጋገር አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል - የሳዑዲ ወታደራዊ ባለሥልጣን

© telegram sputnik_ethiopiaከባዶ የሰላም ወሬ ይልቅ ወደ ተጨባጭ እርምጃ መሸጋገር አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል - የሳዑዲ ወታደራዊ ባለሥልጣን
ከባዶ የሰላም ወሬ ይልቅ ወደ ተጨባጭ እርምጃ መሸጋገር አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል - የሳዑዲ ወታደራዊ ባለሥልጣን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.10.2026
ሰብስክራይብ

ከባዶ የሰላም ወሬ ይልቅ ወደ ተጨባጭ እርምጃ መሸጋገር አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል - የሳዑዲ ወታደራዊ ባለሥልጣን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዓለም አቀፍ ሥርዓት አሮጌ ሕጎች መዳከማቸውንና በወደፊቱ አሠራር ላይ አሁንም ስምምነት አለመደረጉን በመጠቆም፣ የዓለም አቀፍ ውጥረቶች መቀጠል የሰው ልጅን ወደ አሰቃቂ ሁኔታዎች ሊመራው እንደሚችልና ዓለም 'ከህልውና ስጋት አፋፍ' እንድትጠበቅ በቫልዳይ የውይይት ክለብ ባደረጉት ንግግር ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንኑ የፑቱን ማሳሰቢያ አስመልክቶ የሳዑዲ ዓረቢያው ወታደራዊ ባለስልጣን ብሪጋዴር ጄኔራል አብደላ አል-ሻኢ ለስፑትኒክ ዓረብኛ በሰጡት አስተያየት፣ "የሚያስፈልገው ስለ ሰላም ከማውራት ይልቅ ሰላምን ለማረጋገጥ ወደ ተጨባጭ ሥራ መሸጋገር ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

አብደላ አል-ሻኢ እንደገለጹት፣ የዓለም አቀፍ ግጭቶች መቀጠል ዐቢይ ምክንያት "በሃገራት መካከል መተማመን መጥፋት፣ እንዲሁም የጥቅምና የተጽዕኖ ሽሚያ ነው።"

ወታደራዊ ኃላፊው ምን ነጥቦች አነሱ?

ተግባራዊ እርምጃዎች፦ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት ግጭቶች ከተከሰቱ በኋላ የተለመዱ አጠቃላይ መመሪያዎችን ከመደጋገም ይልቅ ግጭቶች እንዳይከሰቱ የሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።

የኃይል ሚዛን ለውጥ፦ ዓለም አቀፉ ሥርዓት ከሁለት ዋነኛ ኃይሎች (አሜሪካና ሶቪዬት ሕብረት) ወደ አንድ ወገን የበላይነት የተሸጋገረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የቻይና ማደግ ከአሜሪካ ጋር አዲስ የተፅዕኖ ፉክክር ፈጥሯል።

የቀጣይ 5-10 ዓመታት ትንበያ፦ በዓለም አቀፍ ኃይሎች መካከል እውነተኛ የእምነትና የትብብር ለውጥ ካልመጣ በቀጣዮቹ ከ5 እስከ 10 ዓመታት ውስጥ ሙሉ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን አዳጋች ይሆናል።

የኒውክሌር አደጋ እና የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት፦ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጥቅም ላይ የዋለው የኒውክሌር መሣሪያ ተራ የንድፈ-ሐሳብ ስጋት ብቻ አይደለም፤ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረትና ጦርነት አደጋውን ሊያባብሰው ይችላል፡፡

የሕግ የበላይነት ክፍተት፦ የዓለም አቀፍ ሕጎች መኖር ብቻቸውን በቂ አይደሉም፤ ዋናው ችግር ሕጎቹ በሁሉም ሀገራት ላይ ያለ ምንም ልዩነት በተጨባጭና በተዓማኒነት አለመተገበራቸው ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0