ትራምፕ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ለማሰንዘር በያዙት እቅድ አሜሪካ ሦስተኛ የጦር መርከቧን እና 9 ሺህ ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መላኳ ተዘገበ

© telegram sputnik_ethiopiaትራምፕ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ለማሰንዘር በያዙት እቅድ አሜሪካ ሦስተኛ የጦር መርከቧን እና 9 ሺህ ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መላኳ ተዘገበ
ትራምፕ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ለማሰንዘር በያዙት እቅድ አሜሪካ ሦስተኛ የጦር መርከቧን እና 9 ሺህ ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መላኳ ተዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.10.2026
ሰብስክራይብ

ትራምፕ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ለማሰንዘር በያዙት እቅድ አሜሪካ ሦስተኛ የጦር መርከቧን እና 9 ሺህ ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ መላኳ ተዘገበ

 

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለማስፋት እያጤኑ ባሉበት በአሁኑ ወቅት፣ የአሜሪካ ጦር ተጨማሪ 9,000 ገደማ ወታደሮችን እና ሦስተኛ አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከብ ወደ መካከለኛው ምስራቅ በመላክ ላይ መሆኑን የምዕራባውያም መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

 

በዚህ ስምሪት ከ7 ሺህ በላይ የባህር ኃይል መርከበኞችን እና 2 ሺህ የየብስና የውሃ ተዋጊዎችን ያሳፈሩ ዩኤስኤስ ቴዎዶር ሩዝቬልት እና ዩኤስኤስ ማኪን አይላንድ የጦር መርከቦች ስብስብ ይገኙበታል። ሦስቱም አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች በቀጣናው የሚቆዩ ከሆነ፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ ተዋጊ አውሮፕላኖች የአሜሪካ የባህር ኃይል ስምሪት ከ20,000 በላይ የባሕር ኃይል ሠራተኞች እና ተዋጊዎች ይደርሳል።

 

ይህ የጦር ኃይል ክምችት ክንውን ትራምፕ የሆርሙዝ ወሽመጥን እንደገና መክፈት እና የኒውክሌር ድርድሩን ማስጀመርን ያካተተውን የቴሕራንን የቅርብ ጊዜ የተኩስ ማቆም ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

 

ከመጪው የኅዳር ምርጫ በኋላ የአየር ድብደባው ሊጠናከር እንደሚችል የተጠየቁት ትራምፕ “ሊሆን ይችላል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0