ሩሲያ እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በባንጉዊ የትብብር ፍኖተ ካርታ ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በባንጉዊ የትብብር ፍኖተ ካርታ ተፈራረሙ

ስምምነቱ የተፈረመው 140 አባላት ያሉት የሩሲያ ልዑክ በተሳተፈበት የመንግሥታት ኮሚሽን ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ መሆኑን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።

ከተፈረሙት ሌሎች ሰነዶች መካከል፦

▪ በጂኦሎጂ እና በከርሰ-ምድር ሀብት ልማት ዘርፍ የተዘጋጀ የሥራ እቅድ፤

▪ በሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት እና በባንጉዊ ዩኒቨርሲቲ መካከል የተደረገ የትብብር ስምምነት ይገኙበታል።

በተጨማሪም የቡንዲቡግዮ ቫይረስን ለመረመር የሚያስችሉ የሩሲያ ምርመራ ማሽኖች እና ቁሳቁሶች ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የጤና ሚኒስትር ፒየር ሶምሴ ተበርክተዋል።

"ዓላማችን በሩሲያ እና በማዕከላዊ አፍሪካ ኩባንያዎች መካከል ያለውን ግንኙነት በተቻለ መጠን ማጠናከር እና የጋራ የትብብር ፕሮግራሞችን ማልማት ነው" ሲሉ የሩሲያ የኢነርጂ ሚኒስትር ሴርጌይ ሲቪሌቭ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0