የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ34 ትሪሊዮን ብር ዋጋ ያለው 8 ቢሊዮን የዲጂታል ገንዘብ ግብይቶችን አድርጓል - የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ34 ትሪሊዮን ብር ዋጋ ያለው 8 ቢሊዮን የዲጂታል ገንዘብ ግብይቶችን አድርጓል - የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ34 ትሪሊዮን ብር ዋጋ ያለው 8 ቢሊዮን የዲጂታል ገንዘብ ግብይቶችን አድርጓል - የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.10.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ34 ትሪሊዮን ብር ዋጋ ያለው 8 ቢሊዮን የዲጂታል ገንዘብ ግብይቶችን አድርጓል - የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ

አኃዙ በሀገሪቱ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እያሳየ ያለውን ፈጣን እድገት የሚያሳይ ነው ያሉት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲጂታል አማካሪ የሆኑት ሚሪያም ሰዒድ በፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ እና በሌሎችም መርሃ ግብሮች የተከናወነው ተግባራት የሀገሪቱን የዲጂታል ፋይናንስ መሠረተ ልማት ይዞታ ለማስፋት እንዳስቻሉ ተናግረዋል።

አማካሪዋ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው 2ኛው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም ላይ ዲጂታል መሠረተ ልማትን በማስመልከት በተካሄደ የፓነል ውይይት እንደተናገሩት፣ ገበያው ለዲጂታል ክፍያ አገልግሎት አቅራቢዎች ክፍት መደረጉና ወጥ አሰራር መዘርጋቱ የሃገሪቱን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለማሳደግ ማስቻሉንም አብራርተዋል።

በሀገሪቱ 158 ሚሊዮን የሚጠጉ የሞባይል ገንዘብ አካውንቶች የተመዘገቡ ቢሆንም፣ አሁንም ንቁ ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ያሉት 30 በመቶ ያህሉ ብቻ እንደሆኑ መገለፁን የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0