አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ወንበር ለማግኘት አንድ መሆን አለባት፤ የምዕራባውያንን 'ከፋፍለህ ግዛ' ስልትም ውድቅ ማድረግ አለባት - ባለሙያው

ሰብስክራይብ

አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ወንበር ለማግኘት አንድ መሆን አለባት፤ የምዕራባውያንን 'ከፋፍለህ ግዛ' ስልትም ውድቅ ማድረግ አለባት - ባለሙያው

በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የአፍሪካ ውክልና መኖር አስፈላጊነት እንጂ ምጽዋት አይደለም፤ አህጉሪቱም ከይግባኝ ባሻገር ወደ ተጨባጭ እርምጃ መሸጋገር አለባት ሲሉ የአፍሪካ ወጣቶች ለሰላምና ደህንነት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አብርሃም ኮርብላ ክሉትሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ከባለሙያው የተሰጡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ወንበር፦ 54 ሀገራት ያሏት አፍሪካ ከዋና ዋና ውሳኔዎች ተግልላ በውሳኔዎቹ እንድትገዛ ልትገደድ አይገባም። ጉዳዩ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ድምፅ አሰጣጥ ከተቃኘ አፍሪካ በቀላሉ ወንበሩን ማሸነፍ ትችላለች።

🟠 ይስሙላ ውክልና አይፈለግም፦ ማንኛውም የአፍሪካ ወንበር ውሳኔዎችን የመሻር (ቬቶ) ሙሉ መብትን ጨምሮ ሙሉ መብት ያለው መሆን አለበት እንጂ ያለ በቂ ውክልና የታዛቢነት ወይም የወሬ ተሳታፊነት ሚና ብቻ መሆን የለበትም።

🟠 የምዕራባውያን የመከፋፈል ስልት፦ የምዕራባውያን የብዝበዛ አጀንዳን የሚፈታተነው ብቸኛው ነገር የአፍሪካ አንድነት መሆኑን ስለሚያውቁ፤  አፍሪካውያንን ለመከፋፈል ማንነትን፣ ብሔረተኝነትን እና የባዕዳን ጠላትን  እንደ መሣሪያ ይጠቀማሉ።

🟠 ወሳኝ ማዕድናት፦ የአፍሪካ ወሳኝ ማዕድናት ቁፋሮ ማውጣት የቅኝ ግዛት ዘመንን የብዝበዛ ዘይቤ ዳግም የሚያያንፀባርቅ መሆን የለበትም። አፍሪካ ጥሬ ዕቃዎችን ከመላክ ባለፈ በምርት ሰንሰለቱ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ያስፈልጋታል።

🟠 ሉዓላዊነት፦ ጋና በቅርቡ ከአሜሪካ ጋር የተደረገውን የጤና አጋርነት ውድቅ ማድረጓ የሚያሳየው የአፍሪካ ሀገራት ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር እና እንደ ሩሲያ እና ቻይና ባሉ አማራጭ አጋሮች ለመጠቀም እየተዘጋጁ መሆናቸውን ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0