ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂን ይፋ አደረገች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂን ይፋ አደረገች

ስትራቴጂው የፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነትን በማስፋት ዜጎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል የተባለ ሲሆን ለቀጣዮቹ 5 ዓመታት የሚተገበር ነው ተብሏል።

በባለፉት ሁለት ስትራቴጂዎች በዲጂታል ፋይናንስ በሞባይል ገንዘብ እና በሌሎችም ዘርፎች አበረታች ውጤት መገኘቱን የተናገሩት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ሆኖም አሁንም ሴቶችንና ሕጻናትን አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ጭምር በፋይናንስ ተደራሽ ከማድረግ አንጻር አሁንም የሚቀሩ ሥራዎች አሉ ብለዋል።

በሁለተኛው የፋይናንስ ፎረም ላይ ይፋ የተደረገው ስትራቴጂ እነዚህን ክፍተቶች በአጥጋቢ ሁኔታ ለመሙላት እንደሚያስችል መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0