ጠላቶቼን አስቀድሜ ለይቼ አውቄያለሁ - ኢብራሂም ትራኦሬ በኅህል ሀገራት ላይ ስለሚሸረቡ ምስጢራዊ ሴራዎች አስጠነቀቁ

ሰብስክራይብ

ጠላቶቼን አስቀድሜ ለይቼ አውቄያለሁ - ኢብራሂም ትራኦሬ በኅህል ሀገራት ላይ ስለሚሸረቡ ምስጢራዊ ሴራዎች አስጠነቀቁ

​የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ወደ ሥልጣን የመጡበትን አራተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ የተወሰኑ የፖለቲካ ተዋንያን ከሳኅል ጥምረት ሀገራት ተጻራሪ ስውር እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

​ትራኦሬ በአምባሳደሯ በኩል ተሳትፎ እንደነበራት ካመነችው ዩክሬን እና "ከጥቂት የፈረንሳይ ጄኔራሎች" ውጭ፤ ቀጣናውን ለማወክ ሙከራ መደረጉን ያመነ የሌላ መንግሥት አካል አለመኖሩን ጠቁመዋል።

​"ጠላቶች እንዳሉን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ከእነሱም ጋር መጋፈጥ አለብን። በጠላት ጉዳይ ወደኋላ ማለት አያስፈለግም። [...] የመረጥነውን የሉዓላዊነት መንገድ ለማስቀጠል እና ፈተናዎችን ለመጋፈጥ መዘጋጀት አለብን" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።



በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0