የሶማሊያ ኃይሎች በባይዶአ የተሰነዘረውን ከባድ ጥቃት በመመከት፤ በአል-ሸባብ እና አጋር ሚሊሻዎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አደረሱ

ሰብስክራይብ

የሶማሊያ ኃይሎች በባይዶአ የተሰነዘረውን ከባድ ጥቃት በመመከት፤ በአል-ሸባብ እና አጋር ሚሊሻዎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አደረሱ

የሀገሪቱ ብሔራዊ ጦር የደቡብ ምዕራብ ክልል አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ባይዶአ ከተማ ላይ የተሰነዘረውን መጠነ-ሰፊ ጥቃት በማያወላዳ መልኩ ማክሸፉን የመከላከያ ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

በፍንዳታዎች የተጀመረው ይህ ጥቃት፤ በአል-ሸባብ* አሸባሪዎች እና ለቀድሞው የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን መሀመድ ላፍታጋሬን ታማኝ በሆኑ ሚሊሻዎች የተቀናጀ ኃይል የተፈጸመ ነው።

የመከላከያ ሚኒስቴሩ መግለጫ እንዳመለከተው፤ የጦር ኃይሉ "ጥቃቱን በጀግንነት በመመከት በአጥቂዎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ" ሲሆን "ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ስር በማዋል  በመሸሽ ላይ የሚገኙትን አማፂያን በማሳደድ" ላይ ይገኛል።

የሽብር ሚሊሻዎች ጥምረት የሞቱትንና የቆሰሉትን ጥለው መሸሻቸው ተዘግቧል።

በላፍታጋሬን እና በፌዴራል መንግሥት መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ውጥረት ምክንያት የፌዴራል ኃይሎች በመጋቢት ወር ባይዶአን ከተቆጣጠሩ ወዲህ በተካታታይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተካሂደዋል። መሰል ጥቃቶች ነሐሴ 11 እና እና ነሐሴ 28 ተመክተው ነበር።

*ከአል-ቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት የታገደ የሽብር ድርጅት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0