የስንዴ አበስብስ በሽታ ኢትዮጵያን እስከ 54% ምርት እያሳጣት እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ

የስንዴ አበስብስ በሽታ ኢትዮጵያን እስከ 54% ምርት እያሳጣት እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ

በሽታው በተለይ ከ2018 ዓ.ም ወዲህ ከባድ ስጋት ሆኖ ብቅ ብሏል ያሉት የግብርና ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ያለው ማዘንጊያ፤ ሀገሪቱ ከ46 እስከ 54% የስንዴ ምርት በበሽታው ምክንያት እያጣች እንደምትገኝ መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

አማካሪው ይህን ያሉት ትኩረቱን በስንዴ በሽታዎች ላይ አድርጎ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስተናጋጅነት በተካሄደው አውደ ጥናት መክፈቻ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ችሎት ይርጋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ "ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ያገኘችውን ውጤት ለማስቀጠል ተባዮችንና የሰብል በሽታዎችን መቆጣጠር አለባት" ብለዋል።

ለዚህ በሽታዎችን ቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም በሽታ የመቋቋም አቅም ያላቸውን አዳዲስ ዝርያዎች በምርምር ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0