የቫልዳይ ስብሰባ ከሶቺ ወደ ሞስኮ ክልል የተዛወረው በተሳታፊዎች ቁጥር መብዛት ነው - የስብሰባው ሊቀመንበር

© telegram sputnik_ethiopiaየቫልዳይ ስብሰባ ከሶቺ ወደ ሞስኮ ክልል የተዛወረው በተሳታፊዎች ቁጥር መብዛት ነው - የስብሰባው ሊቀመንበር
የቫልዳይ ስብሰባ ከሶቺ ወደ ሞስኮ ክልል የተዛወረው በተሳታፊዎች ቁጥር መብዛት ነው - የስብሰባው ሊቀመንበር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.09.2026
ሰብስክራይብ

የቫልዳይ ስብሰባ ከሶቺ ወደ ሞስኮ ክልል የተዛወረው በተሳታፊዎች ቁጥር መብዛት ነው - የስብሰባው ሊቀመንበር

23ኛው የቫልዳይ ዓለም አቀፍ የውይይት ክለብ ዓመታዊ ስብሰባ በዘንድሮው ዓመት ከሶቺ በሞስኮ ክልል እየተካሄደ ያለው ከሎጂስቲክስ ሁኔታዎች ጋር በተያያዙ ምክንያቶች መሆኑን የቫልዳይ ክለብ ልማትና ድጋፍ ፋውንዴሽን ቦርድ ሊቀመንበር አንድሬይ ቢስትሪትስኪ ገልጸዋል።

“እዚህ የተሰበሰብነው ሁሉም ሰው በቀላሉ በርሮ መምጣት እና መውጣት እንዲችል ነው፤ ውሳኔው የተላለፈው በእነዚህ የሎጂስቲክስ ምክንያቶች ነው” ሲሉ ቢስትሪትስኪ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

መግለጫው ‘ፋይናንሻል ታይምስ’ ፕሬዚዳንት ፑቲን የቫልዳይ ክለብ ስብሰባን ከሶቺ ወደ ሞስኮ ክልል ያዛወሩት ከዩክሬን የጥቃት ስጋት የተነሳ ነው ሲል ቀደም ሲል መዘገቡን ተከትሎ የመጣ ነው።

ከመስከረም 18 እስከ 21 የሚካሄደው የቫልዳይ ስብሰባ፤ ከ40 ሀገራት የተወጣጡ 120 ተሳታፊዎችን ያሰባስባል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0