አሜሪካ ለኢራን ግጭት ያፈሰሰችው ገንዘብ በአፍሪካ ለአንድ ዓመት ረሃብን ለመዋጋት ሊውል ይችል እንደነበር የስፑትኒክ ትንተና አሳየ
10:14 28.09.2026 (የተሻሻለ: 10:24 28.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አሜሪካ ለኢራን ግጭት ያፈሰሰችው ገንዘብ በአፍሪካ ለአንድ ዓመት ረሃብን ለመዋጋት ሊውል ይችል እንደነበር የስፑትኒክ ትንተና አሳየ
ስፑትኒክ የተመለከተው የአሜሪካ ኮንግረስ የበጀት ቢሮ ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ አሜሪካ እስከ ሐምሌ 25 ድረስ ለመካከለኛው ምስራቅ ዘመቻ ወደ 38 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ያወጣች ሲሆን ከዛ በኋላ ባሉት እያንዳንዱ ወራት ከ2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ወጪ አድርጋለች።
በአፍሪካ ረሃብን ለማስወገድ እ.ኤ.አ እስከ 2030 ድረስ በየዓመቱ ከ39 እስከ 50 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል ሲሉ የተመድ የእርሻና ምግብ ድርጅት የሩሲያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ኦሌግ ኮቢያኮቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ረሃብን ጨርሶ ለማጥፋት በየዓመቱ 267 ቢሊዮን ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ትልቁን የድጋፍ ድርሻ የምትሻው ከሰሃራ በታች አፍሪካ መሆኗንም አብራርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X