ሩሲያ እና ሲሼልስ የባሕር ደህንነትን ለማጠናከር የጸረ-ባሕር ውንብድና የጋራ ልምምድ ሊያደርጉ ነው

ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ሲሼልስ የባሕር ደህንነትን ለማጠናከር የጸረ-ባሕር ውንብድና የጋራ ልምምድ ሊያደርጉ ነው

ልምምዱ ለመጪው ህዳር ወር የታቀደ ሲሆን ቀጣናዊ የባሕር ደህንነት ስጋቶችን ለማስቆም ከሚደረጉ ጥረቶች አካል መሆኑን የሲሼልስ መከላከያ ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ሜጀር ጄነራል ማይክል ሮሴት፤ የሩሲያ የባሕር ኃይል ማሠልጠኛ መርከብ 'ፔሬኮፕ' በዴሴቲቱ ወደብ መልህቅ መጣሏን ተከትሎ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

የሩሲያ ባለሥልጣናት በወደብ ጉብኝቱ ወቅት ለሲሼልስ ተቋማት ድጋፍ የሚሆኑ አስፈላጊ የምግብ ቁሳቁሶች፣ የህክምና አቅርቦቶች እና መጻህፍትን ያካተተ የሰብዓዊ እርዳታ ጭነት አስረክበዋል።

  ልምምዱ በጋራ ወታደራዊ ሥልጠና እና የካዴት ልውውጥ ላይ ትኩረት አድርጎ በሰኔ ወር የተፈረመውን ስምምነት ተከትሎ የሚመጣ ነው።

የሩሲያ የባሕር ኃይል ምክትል ጠቅላይ አዛዥ አድሚራል ቭላዲሚር ቮሮብዮቭ፤ ኦፕሬሽኑ ከቀጣናው የባሕር ኃይሎች ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር፣ የባሕር ውንብድናን ለመዋጋት እና በምዕራብ ህንድ ውቅያኖስ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0