የኬንያ ላሙ ወደብ ለዳንጎቴ ምስራቅ አፍሪካ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ማስጀመሪያ ከባድ ማሽኖች የጫነች መርከብ ተቀበለ

ሰብስክራይብ

የኬንያ ላሙ ወደብ ለዳንጎቴ ምስራቅ አፍሪካ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ማስጀመሪያ ከባድ ማሽኖች የጫነች መርከብ ተቀበለ

የ2 ሺህ 930 ቶን ከባድ የግንባታ ዕቃዎች ጭነት፤ እሮብ ለሚካሄደው የፕሮጀክቱ የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ትልቅ እርምጃ ነው።

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

🟠 ከ15–17 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣበት እና በቀን 700 ሺህ በርሜል የማጣራት አቅም ያለው የዳንጎቴ ምስራቅ አፍሪካ ማጣሪያ፤ በዋናነት ከኬንያው ሎኪቻር የነዳጅ ጉድጓድ እና ከሌሎች የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ምንጮች ድፍድፍ ነዳጅ ያገኛል።

🟠 ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ በላሙ ወደብ ከፍተኛ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴን በመፍጠር፣ ቀጣናዊ የነዳጅ ሎጂስቲክስ እና የሥራ ዕድል ፈጠራን በማሳደግ እንዲሁም ኬንያን ለጎረቤት ሀገራት የኃይልና የንግድ ማዕከል በማድረግ ለረጅም ጊዜ ሲገነባ የቆየውን የ "ላፕሴት" ኮሪደር ያጠናክራል።

🟠 የ "ላፕሴት" ኮሪደር ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን በወደቦች፣ በየብስ መንገድ፣ በባቡር መስመሮች እና በነዳጅ ማስተላለፊያዎች የሚያገናኝ የ25 ቢሊዮን ዶላር ቀጣናዊ ሜጋ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0