በሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ሲካሄድ የቆየው ዓለም አቀፍ የባሕሎች ኅብረት ፎረም ተጠናቀቀ

ሰብስክራይብ

በሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ሲካሄድ የቆየው ዓለም አቀፍ የባሕሎች ኅብረት ፎረም ተጠናቀቀ

​ ለ12ኛ ጊዜ የተካሄደው ፎረም በቅርስ፣ በዓለም አቀፍ ትብብር እና በአዳዲስ የሥነ-ጥበብ  ቴክኖሎጂዎች ላይ ባተኮሩ ወደ 66 በሚጠጉ መርኃ-ግብሮች፤ ከ70 ሀገራት የተውጣጡ 2,468 ተሳታፊዎች እና 454 ተናጋሪዎችን አሰባስቧል።

​በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ ባሕል የፖለቲካ ውጥረቶች ቢኖሩም ውይይቶችን ለማስቀጠል ሊረዳ እንደሚችል እንዲሁም አንድነት የእያንዳንዱን ሕዝብ ወጎችና ማንነት በመጠበቅ ላይ አተኩሮ ትብብርን መሠረት ያደረገ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

​ ከመስከረም 15-16 የተካሄደው ይህ ፎረም፤ ከባሕሉ ዘርፍ የተውጣጡ ሰዎችን፣ የሳይንስ ሊቃውንትን እንዲሁም የንግድ፣ የመንግሥት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችን አገናኝቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0