አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ሱዳን የአሜሪካ ቪዛ አያስፈልጋትም፤ የፈጥኖ ደራሹን ኃይሉን እናጠፋለን አሉ

ሰብስክራይብ

አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ሱዳን የአሜሪካ ቪዛ አያስፈልጋትም፤ የፈጥኖ ደራሹን ኃይሉን እናጠፋለን አሉ

የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር፤ በኒውዮርክ በተካሄደው 81ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የአሜሪካ ቪዛ በመከልከላቸው ሳይገኙ መቅረታቸውን ተከትሎ በካርቱም በተካሄደ ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ነው ይህን ቆራጥ አስተያየት የሰጡት።

ቁልፍ ጉዳዮች፦

🟠 ሱዳን ምንም ዓይነት ቪዛም ሆነ የውጭ እርዳታ አያስፈልጋትም ያሉት አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን፤ "እዚሁ ሀገሬ ከእናንተ ጋር እሞታለሁ" ሲሉ ለሕዝቡ ተናግረዋል።

🟠 የፈጥኖ ደራሹ ኃይል (አርኤስኤፍ) ሚሊሻዎችን "ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ" እንደሚደመስሱ እና በዓመፀኞቹ የተያዙትን ግዛቶች "እስከ ዳርፉር ድረስ" ነፃ እንደሚያወጡ ዝተዋል።

🟠 የቪዛ ክልከላው ሱዳን የውጭ ድጋፍ እንዳለው ከሚነገርለት የአርኤስኤፍ አማፅያን ቡድን ጋር የሦስት ወር የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ስምምነት እንድትፈራረም በአሜሪካ የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጓን ተከተሎ የመጣ እንደሆነ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

🟠 የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የትኛውም የሰላም ጥረት የውጭ ጣልቃገብነትን የሚያስቀር እና አርኤስኤፍን ሕጋዊ የማያደርግ መሆን እንዳለበት ያሰመረ ሲሆን የሱዳን ሉዓላዊነት ከተከበረ ግን ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0