ላቭሮቭ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የሩሲያን አዲስ የዓለም ሥርዓት እይታ አብራሩ

© telegram sputnik_ethiopiaላቭሮቭ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የሩሲያን አዲስ የዓለም ሥርዓት እይታ አብራሩ
ላቭሮቭ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የሩሲያን አዲስ የዓለም ሥርዓት እይታ አብራሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.09.2026
ሰብስክራይብ

ላቭሮቭ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የሩሲያን አዲስ የዓለም ሥርዓት እይታ አብራሩ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦

🟠 በቁጥር አነስተኛ የሆኑት የምዕራባውያን የቢሊዮኖችን ሰዎች ሕይወት አደጋ ውስጥ ከተዋል፣

🟠 ሩሲያ የቬኔዙዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው በአስቸኳይ እንዲለቀቁና መሰል ድርጊቶች እንዳይደገሙ ዋስትና ትጠይቃለች፣

🟠 የደቡባዊ እና ምስራቅ ዓለም ሀገራት ሉዓላዊ የዕድገት ማዕከላት እየሆኑ ነው፣

🟠 የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ግድያ ተቀባይነት የሌለው የአምባገነናዊነት መገለጫ ነው፣

🟠 የሆርሙዝ ቀውስን ለመፍታት በአረብ ሀገራት እና በኢራን መካከል እምነት መመለስ ያስፈልጋል፣

🟠 በዌስት ባንክ የሠፈራ መስፋፋት ከቀጠለ ለፍልስጤም ሀገር የሚሆን ቦታ አይቀርም፣

🟠 አውሮፓ የዩክሬንን የሰላም ስምምነት ለማስተጓጎል ከምታደርገው ጥረት ባለፈ፤ ኪየቭ በሩሲያ ሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ የምታካሂደውን የድሮን ጥቃት እያገዘች ነው፣

🟠 ሩሲያ ለኩባ አጋርነቷን በማረጋገጥ በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳ ጥሪ ታቀርባለች፣

🟠 ሰርቢያ የአውሮፓ ኅብረትን በአባልነት ለመቀላቀል ሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንድትጥል እየተገደደች ነው፣

🟠 ሩሲያ የልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ግቦችን ታሳካለች፣

🟠 ሩሲያ በብሪክስ፣ በሻንጋይ የትብብር ድርጅት እና በሌሎች ኅብረቶች በኩል አንድ የሚያደርግ አጀንዳ በማንገስ ለዓለም አቀፉ ሁኔታ መፍትሔ ለመፈለግ እየሠራች ነው፣

🟠 ሩሲያ፣ ቤላሩስ እና ተመሳሳይ አቋም የያዙ ሀገራት የዩሬዢያን የብዝሃነት ቻርተር ለመቅረጽ እና የአኀጉሩን ጥቅሞች ለማስጠበቅ የሚያስችል መግለጫ አጽድቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0