ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ወጪ ንግድ በሁለት ወራት ውስጥ 81.7 ሚሊዮን ዶላር ሰበሰበች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ወጪ ንግድ በሁለት ወራት ውስጥ 81.7 ሚሊዮን ዶላር ሰበሰበች

የሁለት ወራት አፈጻጸሙ በ2018 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 68.1 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ13.6 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ20% እድገት እንዳለው ተገልጿል።

 

ለአፈጻጸሙ ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት ዘርፎች ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር አንጻር ዕድገት አሳይተዋል፦

ምግብና መጠጥ የ29%፣

ቆዳ የ2%፣

ጨርቃጨርቅና አልባሳት የ13%።

 

በሌላ በኩል የኬሚካልና ኮንስትራክሽን እንዲሁም የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ዘርፎች ከምርትና የገበያ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ቅናሽ አሳይተዋል ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

 

ኢትዮጵያ በ2019 በጀት ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪ ወጪ ምርቶች 600 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት አቅዳለች፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0