የአፍሪካ ታሪክ፣ ባሕል እና ሉዓላዊነት እንዲያከበር እንፈልጋለን - የሶማሊያ የቱሪዝም ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ታሪክ፣ ባሕል እና ሉዓላዊነት እንዲያከበር እንፈልጋለን - የሶማሊያ የቱሪዝም ሚኒስትር

በሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የባሕሎች ኅብረት ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት ሚኒስትሩ አብዱልፈታህ ካሲም መሐመድ፤ በአፍሪካ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ የሚደረግን የትኛውንም ጣልቃ ገብነት በመቃወም "የአፍሪካ ሕዝቦች ከሁሉም ወገኖች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር" ለትብብር ዝግጁ ናቸው ብለዋል።

ሶማሊያም ከሩሲያ ጋር "በመከባበር ላይ የተመሠረተውን" ትብብር በደስታ ትቀበላለች ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

 

"ሩሲያ በሥልጠና እና ቴክኖሎጂዎች ሶማሊያ የራሷን የመሠረተ ልማት እንድትገነባ ልትረዳ ትችላለች።"

በመንግሥታት ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ እና በሩሲያ ሕዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ለባሕል ልውውጥ ወሳኝ ድልድይ ይከፍታል ሲሉ ሚኒስትሩ አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0