ፖለቲካ በሚከሽፍበት ጊዜ ባሕል እንደ ድልድይ ያገለግላል - ፑቲን
19:58 25.09.2026 (የተሻሻለ: 20:04 25.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፖለቲካ በሚከሽፍበት ጊዜ ባሕል እንደ ድልድይ ያገለግላል - ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሴንት ፒተርስበርግ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የባሕሎች ኅብረት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ግንኙነቶች እክል በገጠማቸው ጊዜ ባሕል ውይይትን ማስቀጠል ይችላል ብለዋል።
ፑቲን በግጭቶች፣ ማዕቀቦች እና ገደቦች ምክንያት ግንኙነቶች በተቋረጡበት ጊዜ ባሕልን ወሳኝ የግኑኝነት መሳሪያ መሆኑን በመጥቀስ፤ "ባሕል በተቃርኖዎች ውስጥ በሰዎች መካከል ድልድይ የመገንባት አቅም አለው" ብለዋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሩሲያ ባሕልን እንደ ልዩ መብት ሳይሆን፤ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ተሰጠ መብትና እድል አድርጋ ትመለከተዋለች።
ሩሲያ ከሌሎች ሀገራት ጋር የጠበቀ የባሕል ትብብር ለማድረግ እና ልምዷን ለማካፈል ምንጊዜም ዝግጁ ነች።
ለሩሲያ ቤተ-መዛግብት፣ ቲያትር ቤቶች እና ቤተ መዘክሮች አዳዲስ የልማት ስትራቴጂዎች እየተዘጋጁ ነው።
ሩሲያ ጥበብን የሚረዱ እና ከዘመናዊው ታዳሚ ጋር መገናኘት የሚችሉ ዳይሬክተሮች፣ አዘጋጆች እና የባሕል ሰዎች ያስፈልጓታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X